ስለ ራሴ

ሌላው ዓለም ላይ ለመድረስ ዛሬ ዓለም የደረሰበት ደረጃ ለይ ለመድረስ እና አብሮ በየደቂቃው እና በየሰዓቱ እእየተለወጠ እና እያደገ ካለው ቴክኖሎሎጂ አብሮ ለመጓዝ የየዕለት ሕየወታችንን እና የሥራ ድካማችንን ለመቀነስ እንዲሁም በአገልግሎት ዘርፍም ቀልጣፋ ለማድረግ ጠቄሜታው ቀላል አይደለም።
በመልካም ፍቃደኝነት እና በቅንነት በመነሳሳት የተማርኩትን እና ያወኩትን ለሌሎች ለማካፈል ይህንን ድህረ ገጽ ለመክፈት ችያለው። ዛሬ አብዛኛው ቴክኖሎጂ ለሁሉም መማር ለሚፈልግ ክፈት ነው ። መማር ለፈለገ ማንኛውም ሰው ክፈት ናቸው በአገራች እውቀት ለማጋራት እና ለማካፈል መንገዶች የሉም ልምዱም የለንም በዚህ ዘንድ በዙ መስራት የጠበቅብናል የሚል ጽኑ እምነት አለኝ። ከእኔ የተሻሉ እውቀት ልምድ ያላቸው በአገር ውስጥ እና ከአገር ውጪ ብዙ እንዳሉ አውቃለው። ይህ ገጽ ለጀማሪዎች ድህረ ገጽ እና ፕሮግራሚግ ገና ለመማር የመጀመርያቸው ለሆነ ታሳቢ አድርጎ የተዘጋጀ ትምህርት ነው ይህ ለProffessionals is not Right Place ። ያላችሁን እውቀት ለማካፈል ግን ከዚህ የተሻለ ቦታ ያለ ያለ አይመስለኝም።

Advertisements