HTML አንድ የኮፒውተር ቋንቋ አካል ሲሆን ድህረ ገጽ መገንባት ወይም ለመፍጠር የምንጠቀምበት ክፍል ነው።የህን ቋንቋ ለመማር በአንጻራዊ መልኩ በጣም ቀላል ነው ከሌሎች የኮፒውተር ቋንቋዎች ስናነጻጽረው። እስከ ዛሬ ድረስ በዙ የእድገት ደረጃዎችን አልፏዋል። በተለይ ከ1991 ጀምሮ እስከ 2014 ድረስ ብዙ መሻሻል ላይ ደርሷል HTML በ1991 ፤ HTML 2.0 በ1995 ፤ HTML3.2 በ1997 ፤ HTML 4.01 በ 1999 ፤ XHTML በ 2000 አልፎ ዛሬ የደረሰበት ደረጃ ማለት HTML 5 በ 2014 ደርሷል። (የቀን አቆጣጠር በፈረጆች መሆኑን ይታወቅልኝ) ።
ይህል ሁሉ ዘመን በማን ስር ነበር መሻሻሎች እንዲደረግበት ሲደረግ የነበረው? ይህን በበላይነት የሚቆጣተረው w3c የሚባል ድርጅት ነው በይህ ድረጅት አማካኝነት ተከታታይነት ባላው መልኩ ቈንቋውን በመከለስ ጊዜው በሚፈቅደው የሚያስፈልገውን መሻሻያ እና ክለሳ እያደረገበት ዛሬ የደረሰበት ደረጃ ላይ አድረሱታለ ለበለጠ ንባብ ስለ w3c

