ምን ሟሟላት አለብን

ድህረ ገጽ ለመማር የሚያስፈልገው በመጀመርያ ሙሉ ፍላጎት እና ተነሳሽነት ነው ከዚህ በመቀጠል የምመክረው ታጋሽ መሆነ ያስፈልጋል ትምህርቱ ይበልጥ በራስ ተነሳሽነት እስከ ሆነ ድረስ ማለቴ ነው ማንም የሚቆጣጠርህ አካል የለም  ከፈለክ ትማራለህ ካልፈለክ ጊዜህን በዚ ድህረ ገጽ ላይ ባታጠፉ ወንድማዊ ምክሬ ነው።

ወደ ዋናው ሐሳቤ ስገባ ትምህርቱን በሙሉ አቅም ለመከታተል የኢተርኔት ግንኙነት ቢኖራችሁ መልካም ነው ። አንዳንድ አጋዥ ፕሮግራሞችን ለማውረድ ስለሚያስችለን ብቻ ሳይሆን ይህን ገጽ ያለ ኢተርኔት መክፈት ስለማይቻል ነው። መሰረታዊ ድህረ ገጽ ምስጥራዊ ቁልፎችን(CODE) ለመጻፍ በላፕቶፓችሁ ወይም ዴስቶፓችሁ ላይ ያለው Notepad መጠቀም ትችላላችሁ እንዴት የሚለው እንይ፡

  1. በመጀመርያ Notepad-ን ይክፈቱ Open Notepad
  2. በመቀጠል File=>>Save as በሚከፈትላችሁ አዲስ ገጽ/ፎርም ላይ የፋይሉን ሥም በማስቀጠል .html ብለው የጻፉ fileName.html
  3. Save የሚለውን ይቻኑት

ለላኛው አማራጭ ደሞ በቀጥታ  ከድህረ ገጽ ላይ በራሳችን ማሽን ላይ በመጫን ነው ይህ Software Notepad++ ይባላል ፡ ኢተርኔት መክፈቻ Browser ከነዚህ ውስጥ የትኛውንም ሊሆን ይችላል Google Chrome, FireFox,Internet explorer, ወይም Opera ሊሆን ይችላል ። ይህንን ተስፈንጣሪ(link) በመከተል Notepad++ ማሽኖት ላይ ይጫኑት download notepad++

እኔ እንደ አዲስ ተማሪዎች የምመክራችሁ ከNotepad++ ይልቅ Notepad ብትጠቀሙ መልካም ነው ምክንያቱም ሙሉ የራሳችሁን የመማር ፍጥነት እና የማስታወት ብቃታችሁን የምታዩበት የምትገመግሙበት የሚያስችላችሁ ስለሆነ ነው ።

 

Advertisements